Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረትና ብሪታኒያ የንግድ ስምምነት ላይ ለመድረስ ውይይታቸውን ዳግም ሊጀምሩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረትና ብሪታኒያ ከፍቺ በኋላ በሚኖረው የንግድ ሂደት ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ያቋረጡትን ውይይት በብራሰልስ ሊጀምሩ ነው።

ብሪታኒያ እና የአውሮፓ ህብረት በአሳ የማስገር መብት እና በንግድ ውድድር ህግ ላይ ያላቸው ልዩነት እንደቀጠለ መሆኑ ይነገራል።

ብሪታኒያ ከህብረቱ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ አሁንም ጊዜ እንዳለ ስትገልፅ በአውሮፓ ህብረት በኩል ይህ ተስፋ ብዙም የለም።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን እና ጠቅላይ የብሪታንያው ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ካልደረሱ ህብረቱ እና ብሪታኒያ በምርቶች ላይ ቀረጥ መጣል እና የድንበር ቁጥጥር እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል።

የኮሚሽኑ ዋነኛ ተደራዳሪ ማይክል ባርነር ለአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች በድርድሩ የልዩነት ነጥቦች ዙሪያ ማብራሪያ መስጠታቸውን ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.