Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር ህልውና፣ ሰላምና ልማት በጋራ መቆም ያስፈልጋል – የመቐለ ሃገር ሽማግሌዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሀገር ህልውና፣ ሰላምና ልማት በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ የመቐለ ከተማ የሃገር ሽማግሌዎች አስገነዘቡ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ህዝብ በማወያየት ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ በመቐለ ከተማም ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በመቐለ ከተማ ከጊዜያዊ አስተዳዳሩ ጋር ውይይት ያደረጉት የሀገር ሽማግሌዎች ለሃገር ህልውና፣ ሰላምና ልማት በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

“ያለችን አንዲት ሀገር ነች፣ ሰላማችንን እውን ማድረግ የምንችለውም እኛው ነን፤ በአንድ ሃገር ላይ ሁለት የተለያየ የታጠቀ አካል ካለ ደግሞ ችግር ያስከትላል” ብለዋል።

በመሆኑም በህወሓት የጥፋት ቡድን በህገ ወጥ መንገድ የታጠቁ የመቐለ ወጣቶች መሳሪያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሠራዊት እንዲያስረክቡ የሃገር ሽመግሌዎች ጠይቀዋል።

የህወሓት ቡድን በጫና በርካታ ወጣቶችን በማስታጠቅ በተለይ በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር መስራቱ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ገልጸዋል።

የሀገር ሽማግሌዎቹ የትግራይ ህዝብ የሚፈልገው ሰላም፣ ልማትና አብሮነትን እንደሆነ ገልጸው፤ የህወሓት ቡድን ወጣቶችን በማስታጠቅ ወደ ግጭትና አለመረጋጋት ማምራቱን አውግዘዋል።

በህገ ወጥ አካል መሳሪያ የታጠቁ ወጣቶች መሳሪያውን በአፋጣኝ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.