የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በ“ስማርት አፍሪካ” የቦርድ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

By Tibebu Kebede

December 07, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በሚመራው የ“ስማርት አፍሪካ” የቦርድ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ ፡፡

ስማርት አፍሪካ በአፍሪካ መሪዎች ተነሳሽነት የተጀመረ በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲፋጠን፣ የአፍሪካን ብሮድባንድ ተደራሽነት እና የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዕድገት የሚያፋጥን ዕቅድ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቷ በኢትዮጵያ የፀደቀውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ እና የተወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!