Fana: At a Speed of Life!

በአውስትራሊያ ሰደድ እሳት ካለፈው ሰኞ ጀምሮ 8 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡባዊ አውስትራሊያ በሰደድ እሳት እስካሁን 8 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።

አድማሱን እያሰፋ ያለው ሰደድ እሳት ባደረሰው ጉዳት ከ200 በላይ ቤቶች መውደማቸውም ነው የተነገረው።

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪም የ2 ሰዎች አድራሻ መጥፋቱንም ፖሊስ አስታውቋል።

በኒው ሳውዝ ዌልስ እና ቪክቶሪያ በተቀሰቀሰው እሳት ሳቢያም በርካቶች መኖሪያ ቀያቸውን ለቀው እወጡ ነው።

ከወር በፊት የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ሲሆን፥ እስካሁን በጥቂቱ 18 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶችም የገቡበት አልታወቀም ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም 916 ቤቶች የወደሙ ሲሆን፥ 363 ቤቶች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው።

ፖሊስም በሰደድ እሳቱ ሳቢያ የሚደርሰው አደጋ ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

በርካቶችም ወደ ባህር ዳርቻዎች በመሸሽ ከእሳት አደጋው ለማምለጥ ጥረት እያደረጉ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.