Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የዲጂታል ጤና ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የዲጂታል ጤና ፎረም ላይ እየተሳተፈች ነው።
 
መድረኩ “ለሁሉም የዲጅታል ጤና አገልግሎትን በማዳረስ የዲጅታል ጤና ማህበረሰብ ለመገንባት እና ፈጣን የጤና አገልግሎት መፍትሄ በመስጠት ማንም ወደ ኋላ እንዳይቀር ማድረግ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
 
በፎረሙ ላይ የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሀመድ የኢትዮጵያ መንግስት በዲጂታል ኢትዮጵያ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል የጤና አገልግሎትን ለመዘርጋት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ኢትዮጵያ ለዲጂታል አሰራር ትኩረት ሰጥታለች ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ስርዓትን ለመዘርጋት ቁርጠኛ መሆኗንም አንስተዋል።
 
አሰራሩን በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና እጥረቶችንም በመድረኩ አብራርተዋል።
 
ነገ በሚጠናቀቀው በዚሁ መድረክ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.