Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ 22 ፕሮጀክት መለየቱን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በ300 ፕሮጀክቶች ላይ ያካሄደውን የፕሮፓዛል ግምገማ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
 
ፈንዱ በፈረንጆቸ መስከረም አጋማሽ ከቀረቡለት 300 ፕሮጀክቶች መካከል ባካሄደው ግምገማ 22 ፕሮጀክቶች መለየቱን አስታውቋል፡፡
 
በቀጣይም የተለዩትን 22 ፕሮጀክቶች የአፈፃፀም አቅም እና የበጀት ግምገማ እንደሚያደርግ ያስታወቀ ሲሆን፥ ግምገማው በተቋማቱ ሃብት ፣ አስተዳደር እና ያቀረቡትን እቅድ ለመፈፀም ባላቸው አቅም ዙሪያ የሚያተኩር ነው፡፡
 
የፕሮጀክቶቹ ፕሮፖዛል ግምገማ በኢትዮጵያ በሚገኙ እና ከዳያስፖራው ማህበረሰብ በተለያዩ ዘርፎች በተሰማሩ በጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያዊያን መካሄዱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ገልጿል፡፡
 
የግምገማው ዋና መስፈርቶችም የቀረበው ፕሮጀክት ቀጣይነት፣ የሚያሳርፈው ተፅዕኖ ፣ ፈጠራ ፣ተጠያቂነት፣ ግልፅነት፣ የማደግ አቅም እና ኮሙዩኒኬሽን ናቸው፡፡
 
የፈንዱ የቦርድ ዳይሬክተር አቶ ዛፉ እየሱስወርቅ በቅድመ ፕሮጀክት ዳሰሳው ለተሳተፉት አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፥ የፈንዱን መስፈርት እና የነጥብ ስርዓቱን ያሟሉ ውጤታማ አና ጥራት ያላቸው ፕሮጀክቶች ተለይተዋል ብለዋል፡፡
 
የመጨረሻዎቹ ድጋፍ የሚደረግላቸው ፕሮፓዛሎች ከመለየታቸው በፊት በገለልተኛ አማካሪዎች የተቋማቱ አቅም እና በጀት ግምገማ እንደሚደረግም ገልፀዋል፡፡
 
በመጀመሪያው ዙር የተሻሉ ተብለው ለተመረጡ ፕሮጀክቶች 4 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን፥ ዝቅተኛው ድጋፍ 6 ሚሊየን 400 ሺህ ብር እንዲሁም ከፍተኛው 11 ሚሊየን 200 ሺህ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
 
አሸናፊ ፕሮጀክቶቹ ከአንድ ወር በኋላ ይፋ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.