Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስዊዲንና ሌሎች የኖርዲክ ሀገራት ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ካይ ሱዌር ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ውቅትም የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ስላካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደር ድሪባ ኩማ በዚሁ ወቅት፥ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ስላካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ የገባው ተገዶ እንደሆነ በመግለፅ፤ ይህ የሆነውም ልዩነቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ፍቃደኛ ባልሆነው የወንጀለኛው የህወሓት ቡድን ምክንያት ነው ብለዋል።

ህግ የማስከበር ዘመቻው በስኬት እንደተጠናቀቀ በማብራሪያቸው ያነሱት አምባሳደር ድሪባ፥ መንግስት ሲቪል ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጉንም ገልፀዋል።

የዘመቻውን መጠናቀቅ ተከትሎም መንግስት በትግራይ ክልል በሚያካሂደው የመልሶ ግንባታ ስራ ላይ ፊንላንድ እና ሌሎች አጋር ሀገራት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንዲሆኑም አምባሳደር ድሪባ ጥሪ አቅርበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.