Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 29 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ10ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
የትምህርት መርሀግብሩን ለማስቀጠል የሀገር ሰላም ወሳኝ መሆኑን የገለፁት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊየን ማቲዮስ÷ መስሪያ ቤቱ የመከላከያ ሰራዊቱ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ያደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
የትምህርት ሚኒስትርም እንደ ተቋም መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ የ10ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን እና በቀጣይም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል።
የገንዘብ ስጦታውን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ ትምህርት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
ከዚህ ቀደም “ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ደም መለገሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.