Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ከ8 ፕላን አስተግባሪ ተቋማት ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን መዋቅራዊ ፕላንን በአግባቡ ለማስፈጸም ከስምንት ፕላን አስተግባሪ ተቋማት ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ።

የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ከአዲስ አበባ መንግዶች ባለስልጣን፣ ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ፣ ከመሰረተ ልማት ቅንጅትና ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከመሬት ይዞታና መረጃ ኤጀንሲ፣ ከትራንስፖርት ቢሮ፣ ከውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና የአካባቢ ጥበቃና ልማት ኮሚሽን እንዲሁም የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽህፈት ቤት ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል።

የውል ስምምነቱ በአዲስ አበባ ከተማ ከመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ቅንጅት ጋር በተያያዘ የሚስተዋለውን  ችግር ለመፍታት  እንደሚያግዝ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር መስከረም ምትኩ ገልጸዋል።

በከተማው የሚገኙ የልማት ተቋማት ከፕላን ጋር በተያያዘ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በጋራ ለመፍታት እና በግንባታ ሂደት የሚያጋጥሙ መጓተቶችን ለመፍታት እንዲሁም አላስፈላጊ ወጪዎችን ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል።

በተጨማሪም የልማት እንቅስቃሴው በመሪ ፕላኑ መሰረት የማስፈፀም፣ ህግና መመሪያ በጋራ በአግባቡ ለመተግበር እንደሚያግዝ ዶክተር መስከረም መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሰክረተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.