በኦሮሚያ ክልል የገዳ ሥርዓት እንደ አንድ የትምህርት አይነት መሰጠት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገዳ ሥርዓት አንድ የትምህርት አይነት መሰጠት ተጀምሯል።
ትምህርቱ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በሁሉም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል መስጠት መጀመሩን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቅዋል።
ከ500 ሺህ በላይ የገዳ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍት እና የመምህራን መመሪያ ታትመው ለትምህርት ቤቶች መከፋፈላቸውንም አስታውቅዋል።
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥናት የገዳ ሥርዓተ ትምህርት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ቢሰጥ በሕዝቡ ማኅበረ-ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በማረጋገጣቸው ትምህርቱ መጀመሩ ተገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡–
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!