Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከአልጄሪያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአልጄሪያ የኢፌዴሪ ልዩ መልእክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከአልጄሪያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ፍርሃት አይት አሊ ብራሂም ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ አምባሳደር ነብያት፥ የፌደራል መንግስት ሕግንና ሥርዓትን በማስከበር እንቅስቃሴው አጥፊው ቡድንና የሕወሓት ጁንታ የተቆጣጠረውን የትግራይ ክልል ዜጎች ለጉዳት ሳይጋለጡ በኃላፊነትና በጥንቃቄ በአጭር ጊዜ ነፃ ለማውጣት መቻሉን አብራርተዋል።

በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት እንዲመለሱ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

አምባሳደር ነብያት አክለውም ኢትዮጵያና አልጄሪያ ያላችውን ጠንካራ ፖለቲካዊ ግንኙነት በኢኮኖሚውም መስክ መድገም እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በተለይም የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና መመስረት ውጤታማ ለማድረግ በአፍሪካ በኢንዱስትሪው መስክ ተባብሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የአልጄሪያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ፍርሃት አይት አሊ ብራሂም በበኩላቸው፥ ለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው፤ ሰላምና መረጋጋት ለዕድገት አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰው መንግስት ህግና ስርዓት ለማስከበር የወሰደው እርምጃ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያና አልጄሪያ በኢንዱስትሪ መስክ ተባብረው መስራት እንዳለባቸውና ልምድና ተሞክሯቸውንም በመለዋወጥ ለህዝባቸው ማዋል እንደሚገባቸውም አውስተዋል።

ሁለቱ ሃገራት በመስኩ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ሁኔታዎች ለማመቻቸት እንዲረዳ በሁለቱ ሀገራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል ቅርብ ግንኙነት የሚያጠናክር አሰራር ለመዘርጋት በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር ቀጣይ ውይይቶችን ለማድረግ ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት ዝርዝር ስራዎችን ለመስራት ከስምምነት መደረሱን በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.