Fana: At a Speed of Life!

ባይደን በመቶ ቀናት ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባት ለመስጠት ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጆ ባይደን በመጀመሪያዎቹ መቶ የስልጣን ቀናቶች ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባት ለመስጠት ቃል መግባታቸው ተሰምቷል፡፡

አዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በመጀመሪያዎቹ መቶ የሥልጣን ቀናቶቻቸው መቶ ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለዜጎች ለመስጠት ማቀዳቸው ተነግሯል፡፡

በመጀመሪያዎቹ የስልጣን ወራት ወረርሽኙ የማያቆም መሆኑን የገለጹ ሲሆን ስትራቴጂው ላይ ጥቂት ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡

በማብራያቸውም የኮቪድ-19 አካሄድን እቀይራለሁ ብለዋል፡፡

ስልጣናቸውን በሚረከቡበት በፈረንጆቹ ጥር 20 ቀን የጤና ቡድኑን እንደሚያስተዋውቁ ገልጸው አሜሪካውያን ለ “100 ቀናት ያህል የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ያድርጉ” ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት ብሪታንያ ለዜጎቿ ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ የተባለ የኮቪድ 19 ክትባት መስጠት መጀመሯ ይታወሳል፡፡

እስካሁን በአሜሪካ ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ሲያዙ ከ285 ሺህ በላይ ሰዎች ህይዎት ለህልፈት መዳረጉ ተወስቷል፡፡

እስካሁን በአለም ዙሪያ ከ68 ሚሊየን 568 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና ዎርልዶ ሜትር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.