የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Tibebu Kebede

January 01, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ በዛሬው ዕለት በደረሰ የመኪና አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው ከመንዲ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ ከነቀምት ወደ ጊዳሚ ወረዳ ሲጓዝ ከነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው ተብሏል።

በአደጋው የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 6 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በጊምቢ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የምዕራብ ወለጋ ዞን ትራፊክ አደጋ ዲቪዥን ሃላፊ ሳጅን ጌጃሶ አበራ ገልጸዋል።