Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በ2012 ዓመተ ምህረት በጅማ ዞንና ከተማ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ተደረገላቸው።
በዞኑና በከተማው ለ288 ሺህ 66 ሰዎች የኤችአይቪ ኤድስ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን÷ምርመራ ከተደረገላቸው ውስጥ 654 ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው መገኘቱ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት 7ሺህ 194 ሰዎች የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሀኒት እየወሰዱ መሆኑን በዞኑ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የተላላፊ በሽታዎች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ፉአድ ሳቢት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
የቫይረሱ ስርጭት ከዚህ ቀደም መቀነስ ቢታይበትም ከቅርብ አመታት ወዲህ መዘናጋት በመፈጠሩ ስርጭቱ እየጨመረ መምጣቱም ነው የተገለጸው ።
በጅማ ዞንና በጅማ ከተማ ዛሬ የኤች አይ ቪ ስርጭት በተመለከተ የመወያያ ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል።
በፅሁፉም የሺሻ እና የጭፈራ ቤቶች መስፋፋት ለቫይረሱ ስርጭት መልካም አጋጣሚ መፍጠራቸው ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ÷ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ የሚያስከትለውን ይህን ቫይረስ ለመከላከል የሃገር ሽማግሌዎች ፣ የእምነት አባቶችና የመንግሥት ተቋሟት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
በሙክታር ጠሃ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.