Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያ ምዕራፍ የዳጉይሩ ጋላፊ የመንገድ እድሳት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ያለውን የትራስፖርት መሳለጥ እንደሚያሻሽል ተስፋ የተጣለበት የመጀመሪያ ምዕራፍ የዳጉይሩ ጋላፊ የመንገድ እድሳት ተጠናቆ ተመረቀ።
የመንገድ ፕሮጀክቱ በወቅቱ እና የአሽከርካሪዎችን ደህንነት ተጠብቆ በከባድ ተሸከርካሪዎች ምርቶችን ለማዘዋወር የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
20 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የመጀመሪያው ዙር የመንገድ እድሳት ባለፈው እሁድ መመቀሩን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በጃፓን መንግስት የሚደገው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 100 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል ተብሏል።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የመንገድ እድሳቱ የከባድ እና መከካለኛ ተሸከርካራች የትራፊክ በመጨናነቅ የሚወስድባቸውን ጊዜ ይቀንሳል ብለዋል።
ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ጠንካራ የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።
ቀሪ 80 ኪሎ ሜትር የመንገድ እድሳት እንደተጀመረ ነው የተጠቆመው።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.