Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በፓርቲው አሰራር፣ አደረጃጀትና ቀጣይ ተልዕኮ ላይ ውይይት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በፓርቲው አሠራር አደረጃጀትና ሀገራዊና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
 
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ መድረኩ የተዘጋጀው የሀገር ክህደት የፈፀመው የጁንታ ቡድን በህግ ማስከበር በተወገደበት ማግስት በመሆኑ አመራሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንድይዝ ያስችላል ብለዋል።
 
በሀገራዊ፣ ክልላዊና አከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታ ላይ በመወያየትና የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ለቀጣይ ተልዕኮ አመራርና አባላት የሚያዘጋጁ እቅዶችን ይዞ እንደሚወርዱም ገልፀዋል።
 
ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ አሰራር፣ አደረጃጀትና ተልዕኮ መመሪያና በፓርቲው ሩብ ዓመት አፈፃፀም እንዲሁም ቀሪ ወራት እቅድ ላይ በመወያየት አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.