Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ ኮርያና ከአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ ኮርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንግ ኪዩንግ-ዋሃ እና ከአየር ላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳይመን ኮቭኒይ ጋር ተወያዩ፡፡

አቶ ደመቀ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ የጥፋት ኃይሉ ህወሓት ኢትዮጵያውያን ተስፋ ያደረጉትን ለውጥ ለመቀልበስ እየሰራ እንደነበረ አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም የጥፋት ኃይሉ ጥቅምት 24 በሰሜን ዕዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የመንግስት ትዕግስት ተማጦ በማለቁ ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ መግባቱን አስታውሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ህግ የማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁን የገለጹት አቶ ደመቀ በክልሉ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን ዳግም ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም አቶ ደመቀ ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምዕራፉም መቀጠሉን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ አብራርተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.