Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት በአዲስ አበባ ስቱዲዮው የቀጥታ የዜና ስርጭት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ መገናኛ ብዙኀን ድርጅት ከአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ስቱዲዮው የዜናና ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በአጀማመር ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸው ነው የተገለጸው፡፡

የአብመድ ቦርድ ስራ አመራር የሆኑት አቶ አገኘሁ የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት ለክልሉና ለሀገሪቱ ህዝቦች ወቅታዊና ተዓማኒ መረጃዎችን በማድረስ አኩሪ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል፡፡

በቀጣይም በአዲስ አበባ ራሱን የቻለ የሚዲያ ማዕከል ለመገንባት እንዲሁም በተለያዩ ቋንቋዎች ፕሮግራሞችን ለመጀመርና የቴሌቪዥን ቻናል እና የኤፍ.ኤም ጣቢያዎችን ለመክፈት መታቀዱን ጠቅሰዋል፡፡

የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት የአዲስ አበባ ስቱዲዮ የቀጥታ ስርጭት ማስጀመር ስነስርዓት ላይ ለድርጅቱ ድጋፍ ያደረጉ የተለያዩ አካላት ታድመዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት ለድርጅቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱ የስራ ኃላፊችዎች  ዕውቅና መስጠቱን አብመድ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.