Fana: At a Speed of Life!

በኮቪድ 19 ክትባቶች ላይ ያነጣጠሩና በድረ-ገፅ ሊሠሩ የሚችሉ የተደራጁ የወንጀል ስጋቶች እንደሚኖሩ ኢንተርፖል አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 30 ፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንተርፖል በ194 አባል ሀገራቱ ለሚገኙ የህግ አስከባሪ አካላት በኮቪድ 19 ክትባቶች ላይ ያነጣጠሩና በድረ-ገፅ ሊሠሩ የሚችሉ የተደራጁ የወንጀል ስጋቶች እንደሚኖሩ ማስጠንቀቁን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ወረርሽኙ ታይቶ የማይታወቅና አጥፊ የወንጀል ባህሪ ያስነሳ በመሆኑ ከኮቪድ 19 እና ከጉንፋን ክትባቶች ጋር በተያያዘ የተሳሳተ የስርቆትና የህገ-ወጥ ማስታወቂያ የወንጀል እንቅስቃሴዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አሳስቧል፡፡

ይህ ሁኔታ ግለሰቦች የሀሰት ክትባቶችን ሲያስተዋውቁ፣ ሲሸጡና ሲያስተዳድሩ የነበሩበትን የወንጀል ምሳሌዎች ያጠቃልላል ብሏል፡፡

በርካታ የኮቪድ 19 ክትባቶች ፀድቀው ወደ ዓለም አቀፍ ስርጭት የሚገቡበት ሁኔታ የተቃረበ በመሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ደህንነት ማረጋገጥና ሀሰተኛ ምርቶችን የሚሸጡ ህገ-ወጥ ድረ-ገፆችን መለየት አስፈላጊ ጉዳይ ይሆናል ተብሏል፡፡

ክትባቶች የተደራጀ ወንጀል ዋና ዒላማ መሆናቸውን የገለፀው ኢንተርፖል በህግ አስከባሪና በጤና ተቆጣጣሪ አካላት መካከል የሚኖረው ቅንጅት የግለሰቦችና የማህበረሰቡ ደህንነት እንዲጠበቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ነው ያለው

‹‹መንግስታት ክትባቶችን ለማውጣት ሲዘጋጁ የወንጀል ድርጅቶችም በአቅርቦቱ ሰንሰለቶች ውስጥ ሰርገው ለመግባት ወይም ሂደቱን ለማደናቀፍ ያቅዳሉ››  ሲሉ የኢንተርፖል  ዋና ፀኃፊ ጀርገን ስቶክ ተናግረዋል።

የወንጀል ኔትዎርኮች የማያውቁ የህብረተሰብ ክፍሎችን ዓላማ አድርገው በሃሰተኛ ድረ-ገፆቻቸው ሐሰተኛ ፈውሶችን በመዘርዘር በጤናና በህይወታቸውም  ላይ ከፍተኛ አደጋን ሊያስከትሉ ይችላሉ ብሏል በመግለጫው፡፡

ዋና ፀኃፊው ‹‹ከኮቪድ 19 ክትባት ጋር የተዛመዱ ሁሉንም ዓይነት የወንጀል ድርጊቶች ለመቆጣጠር ህግ አስከባሪ አካላት የተቻለውን ሁሉ ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተያያዘም ዓለም አቀፍ በረራ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ምርመራው እየተጠናከረ ስለሚሄድ ያልተፈቀደና ሃሰተኛ መመርመሪያ መሣሪያዎች ሊሰራጩ ስለሚችሉ ከቫይረሱ ምርመራ ጋር የመመርመሪያ መሣሪያ ህጋዊነት ማረጋገጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም አስታውቋል።

በመሆኑም የኮቪድ 19 ክትባቶችን መመርመሪያ መሣሪያዎችንና መድኃኒቶችን ኦን-ላይን መድኃኒት የሚያዙ ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

ለህይወት አስጊ የሆኑ ምርቶችን ማዘዝ ከሚያስከትላቸው አደጋዎች በተጨማሪ በኢንተርፖል የሳይበር ወንጀል ክፍል የተሰጠው ትንታኔ በህገወጥ መድኃኒችና ህክምና መሣሪያዎች ይሸጣሉ ተብለው ከተጠረጠሩ የመስመር ላይ ፋርማሲዎች ጋር ከተገናኙ 3 ሺህ ኔትዎርኮች መካከል 1 ሺህ 700 ገደማዎቹ የሳይበር ማስፈራሪያዎችን በተለይም አስጊ እና አይፈለጌ መልዕክት አዘል ማልዌር ይዘዋል ተብሏል።

በመስመር ላይ ማጭበርበሮች ሰለባ ላለመሆን ብዙውን ጊዜ ለእውነት በጣም ጥሩ ለሚመስሉ ቅናሾች ንቁዎች መሆን መጠራጠር እና ደህንነታቸው ማረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ የቅርብ ጊዜውን የጤና ምክር ለማግኘት ሁልጊዜ ከብሔራዊ የጤና ባለስልጣኖች ወይም ከዓለም የጤና ድርጅት ማረገጋጥ እንደሚገም ተጠቁሟል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.