ባለፉት 24 ሰዓታት 568 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 2 ሺህ 296 ሰዎች አገግመዋል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 30 ፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4 ሺህ 313 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 568 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 114 ሺህ 834 መድረሱ ነው የተገለፀው።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 2 ሺህ 296 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 87ሺህ 244 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
እንዲሁም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 769 ደርሷል።