Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በግንባታ ላይ ያለውን የአትክልት መገበያያ ስፍራን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዝሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በግንባታ ላይ ያለውን የአትክልት መገበያያ ስፍራን ጎበኙ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የአትክልት መገበያያ ስፍራ የግንባታ ሂደትን ተዘዋውረው የጎበኙት ምክትል ከንቲባ  ወይዝሮ አዳነች በመጀመሪያው ምዕራፍ እየተገነቡ ያሉ አብዛኛው የመገበያያ ሼዶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ተመልክተዋል፡፡

ከቀጣይ ሳምንት በኋላም በጃንሜዳ የሚገኙ የአትክልት ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ የማንሳት ስራ እንደሚሰራ  ወይዝሮ አዳነች ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአንድ ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን የአትክልት የገበያ ማዕከል 80 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በመጀመሪያው ምዕራፍ ከሚገነቡት 14 ሼዶች እያንዳንዱ ሼዶች 70 ሜትር በ6 ነጥብ 6 ሜትር ስፋት 588 የመገበያያ ሱቆች እንደሚኖሩት ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.