Fana: At a Speed of Life!

ባለፈዉ 1 ወር  ኦነግ ሸኔ ላይ በተወሰደ እርምጃ 370 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ባለፈዉ አንድ ወር  ኦነግ ሸኔ ላይ ሲወስድ በነበረዉ እርምጃ 370 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸው ተገለፀ፡፡

እንዲሁም 176 የቡድኑ አባላት ሲማረኩ፤ 154 በህዝቡ መያዛቸዉን የኦሮሚያ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት አስታዉቋል፡፡

በዚሁ ወቅት ትጥቅና ስንቅ ለሽፍታዉ ሲያቀርቡ የነበሩ 183 የጁንታው የህወሓት አባላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በሎጂስቲክ በኩል 4 ብሬኖችን ጨምሮ 1 ሺህ 585 ጠመንጃዎች፣ 10 ሺህ 902 ጥይቶች፣ 605 የቁም ከብቶች፣ 353 ፍየሎች፣ 54 የጋማ ከብቶች፣ 48 ግመሎች፣ 682 ሺህ 680 ብር እና 204 ሺህ 400 የሀሰት ገንዘብ መያዙን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.