Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ የኤሌክትሪክ ሀይል በቀናት ውስጥ ይመለሳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመቐለ ከተማ የኤሌክትሪክ ሀይል በቀናት ውስጥ እንደሚመለስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የሰሜን ሪጅን አስታውቋል።

በጽንፈኛው የህወሓት ቡድን በከባድ መሳሪያ የተመቱ የከፍተኛ ሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ቀጥሎ የተለያዩ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሀይል ዳግም እያገኙ ነው።

ቡድኑ ከአለማጣ መቐለ ከተዘረጋው 141 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ውስጥ 25 በመቶው ላይ ጉዳት አድርሷል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የሰሜን ሪጅን የትራንስሚሽን ጥገና ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አየልኝ እንደተናገሩት፥ ከሁሉም ሪጅን የተውጣጡ 120 የጥገና ባለሙያዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ስርጭቱን ዳግም ለማስጀመር ርብርብ እያደረጉ ነው።

በዚህም ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚጠጋው ጉዳት የደረሰበት መስመር መጠገኑን ነው ያነሱት።

ይህን ተከትሎም ኮረም እና ማይጨውን ጨምሮ በአብዛኞቹ የደቡባዊ ዞን ከተሞች የኤሌክትሪክ ሀይል ስርጭት መመለሱን ሀላፊው ገልፀዋል።

መቐለ ከተማ እና አካባቢውም በአጭር ጊዜ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሀይል ያገኛል ነው ያሉት።

የመልካ ምድር አቀማመጡ ፈታኝ መሆን የጥገና ስራውን በሚፈለገው ፍጥነት እንዳይሄድ አድርጎታል ብለዋል።

ከአለማጣ መቐለ ድረስ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑን ያነሱት አቶ ሙሉጌታ፥ መቀሌ እና አካባቢው የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያገኙ ከተደረገ በኃላ ወደ አድዋ፣ አዲግራት፣ ሽሬ፣ ሁመራ እና ሌሎች ከተሞች የጥገና ስራው ይቀጥላል ብለዋል።

በፋሲካው ታደሰ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.