Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አልጄሪያ የፓርላማ ለፓርላማ ግንኙነት ማጠናከር እንዳለባቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና አልጄሪያ የፓርላማ ለፓርላማ ግንኙነት ማጠናከር እንዳለባቸው ተገልጿል።

በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከአልጄሪያ የህዝብ ተወካዮች ፕሬዚዳንት ቼኒን ስሊማን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ አምባሳደር ነብያት ኢትዮጵያና አልጄሪያ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ያላቸው ሃገራት መሆናቸው አንስተዋል።

ይህንን ጠንካራ ግንኙነት በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ሁሉን አቀፍ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

አልጄሪያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጉልህ ሚና ያላት ሀገር እንደመሆኗና ከኢትዮጵያ ጋርም በተለያዩ ጉዳዮች የጋራ አቋም የሚያራምዱ በመሆኑ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሁለቱ ሀገራት መካከል የፓርላማ ግንኙነት ማጠናከር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንም አውስተዋል።

የአልጄሪያ የህዝብ ተወካዮች ፕሬዚዳንት ቼኒን ስሊማን በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት በአግባቡ የሚገነዘቡ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ፓርላማዎች ግንኙነት ለማጠናከርም የጉብኝት ልውውጥ ማድረግና በየጊዜው መገናኘት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

በኢትዮጵያና በአልጄሪያ መካከል ፓርላሜንታዊ ዲኘሎማሲ ለማጠናከር የሚረዱ የጉብኝት ልውውጦችን ለማድረግ በውይይቱ ወቅት መግባባት ላይ መደረሱን ከአልጀሪያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.