Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልኡካን የጋና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂደትን ተከታተሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል እና ሰራተኞች የጋና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂደትን ተከታተሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር ፍቅሬ ገብረህይወት የተመራው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰራተኞች ቡድን ነው የጋና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂደትን የተከታተለው።
በቆይታቸውም የጋራና ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሂደትን፣ የድምጽ መስጫ ቀን የተደረጉ ተግባራትን፣ የኮቪድ ወረርሽን በመከላከል የተከናወነውን የድምጽ መስጠት ሂደት ተመልክተዋል።
እንዲሁም ምርጫን የኮቪድ ወረርሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ለማከናወን የተደረጉ ተግባራትን፣ የምርጫ አስፈጻሚው ተቋምን አሰራር፣ የምርጫ ክልል ደረጃ ውጤት ቆጠራ፣ ድመራ እና ይፋ የማድረግን ሂደቱንም ተመልክተዋል።
ከጋና ምርጫ ኮሚሽን አመራር አካላትም ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውነም ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልኡካን ምርጫውን ከመታዘብም በተጨማሪ በተለይ በኮቪድ ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ ሆኖ ምርጫ ማከናወን የሚያስፈልጉትን የበጀት እና የሎጄስቲክስ ዝግጅቶችን ከጋና ምርጫ ልምድ መቅሰም መቻላቸውንም ቦርዱ አስታውቋል።
የጋራ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሰኞ ህዳር 28 ቀን 2013 መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፥ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫውም የ 76 ዓመቱ ናና አኩፎ አዶ 51 ነጥብ 6 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውም ታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.