Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚዘረጉ የመንገድ ልማት ቀጣይ እቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚዘረጉ የመንገድ ልማት ቀጣይ እቅድ ፣የክልሎች ሚና እና ተሳትፎ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ።
በውይይት መድረኩ ላይ የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ፣ የሲዳማ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣ የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ ፣ የኢመባ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የክልል የስራ አመራሮች ታድመዋል።
በመድረኩ ላይ የቀጣይ የአስር አመታት የሀገሪቱ የመንገድ መሪ እቅድ ዋና ዋና ይዘትን የዳሰሰ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
ከባለፋት አመታት የመንገድ መርሃ -ግብሮች አተገባበር የነበሩ ውስንነቶችን በመለየት፣ ቀጣይ የኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት አውታር ሊኖረው የሚችለውን ጸጋዎች አሟጦ ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ በጥልቀት መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ከዚህ አኳያ በመንገድ ግንባታ ሂደት ውስጥ ክልሎችን በአደረጃጀት ፣በመዋቅር ፣በአቅም ግንባታ አሳድጎ የመሰረተ ልማት አውታሩን በከፋተኛ ደረጃ ለማሳለጥ መሪ እቅዱ የጎላ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታና በቀጣይ ከሚኖረው ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ የክልሎችን አቅም አሳድጎ ፣ቀጥተኛ የመንገድ ግንባታ እና ፕሮጀክቶችን ወደ ማስተዳደር የሚያሸጋግር በመሆኑ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ርእሳነ መስተዳድሮቹ አንሰተዋል።
የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና የሲዳማ ክልል ርእሰ መስተዳድርአቶ ደስታ ሌዳሞ በእቅድ ግብአትነት ሊካተቱ ይገባቸዋል ያሏቸውን አንኳር ነጥቦችንም አንስተዋል።
እንዲሁም በቀጣይ ሊተኮርባቸው በሚገቡ አጀንዳዎች ላይም ውይይት ተገርጓል ።
የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ÷ መሪ እቅዱ ክልሎችን በቀጥታ የመንገድ የመሰረተ ልማት ግንባታ ባለቤትና ተቆጣጣሪ በማድረግ ፣ አንድ ተቋም ላይ ተንጠልጥሎ የቆየውን ከፍተኛ የስራ ጫናን ወደ ክልሎች በማጋራት ፣ የመንገድ አውታሩን በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት ለመከወን እንደሚያስችል አብራርተዋል።
የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ በበኩላቸው ÷መሪ እቅዱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ብልጽግናዎችን ለማጎናጸፍ ሚናው የላቀ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተለይም የክልሎችን ሚና እና ሃላፊነት በግልጽ አስቀምጦ ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ፣ የነበሩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ለሀገራዊ የመንገድ የመሰረተ ልማት ግንባታ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ እንደሆነም ተናግረዋል።
ይህን ተፈጻሚ የሚያደርጉ ዝርዝር የፖሊሲና የህግ ማእቀፍችን መንግስት እያዘጋጀ እንደሆነም ገልጸዋል።
ከዚያም ባለፈ በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ በቀጣይ ወደ ግንባታ የሚሸጋገሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በዝርዝር ቀርበዋል።
እንዲሁም በግንባታ ላይ የሚገኙ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጻምና እያጋጠማቸው ያሉ ተግዳሮቶች ላይም ምክክር ተካሂዶል።
በተለይም ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ችግሮችን ይበልጥ ተናቦ ለመፍታት የጋራ አቅጣጫን መቀመጡን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.