Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ዶክተር አብርሃም በላይ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ።
ዶክተር አብርሃም በሰጡት መግለጫ÷ በክልሉ አሁን ላይ የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራው በስፋት መካሄድ መጀመሩን ገልጸዋል።
በክልሉ የተያዩ ከተሞች ድጋፍና እርዳታውን የማከፋፈል ስራው መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ በሽሬ እንደስላሴ እና አላማጣ ከተሞች ለነዋሪዎች ድጋፉ እየተሰጠ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሌሎች የክልሉ ከተሞች ለመድረስ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በትላንትናው እለት ወደ ሽሬ ከተማ ብቻ በ44 የጭነት መኪና የተላከው ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች በስፍራው መድረሱ ይታወቃል።
በዛሬው እለት ደግሞ በ30 የጭነት ተሽከርካሪዎች የተጫነ የድጋፍ እህል መቀሌ ደርሷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.