Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ጁንታ ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብቶች አያያዝ አስከፊዋ እንድትባል አድርጓታል- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የህወሓት ጁንታ የጥፋት ቡድን ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብቶች አያያዝ አስከፊዋ እንድትባል ማድረጉን የሰብአዊ መብት ተሟጋችና የህግ ምሁራን ተናገሩ።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬት ያነጋገራቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋችና የህግ ምሁራን እንዳሉት፥ ቡድኑ ኢ ሰብአዊ ድርጊትን ለመፈፀም የሚያስችሉ አፋኝ ህጎችን ጭምር በማውጣት አለም አቀፍ ወንጀል ፈፅሟል።
የሰብአዊ መብት ተማጋችና የህግ ባለሙያ አቶ ቁምላቸው ዳኜ፥ የህጋዊነት ካባ ደርቦ ኢ ሰብአዊ ድርጊቶችን በዜጎች ላይ ለመፈጸም ስልጣን ላይ በነበረበት ዓመታትም ሆነ በውድቀቱ አፋፍ ላይ ቆሞ ደጋግሞ ተግብሮታል።
ተቋማዊ መልክ ባላበሱት ይህ የኢ- ሰብአዊ ተግባራቸው ዜጎች ተሰቃይተዋል ዋጋ ተከፍሏልም ሲሉ ተናግረዋል።
የህውሃት ጁንታ ከስልጣን ከተባረረ በኋላም ቢሆን የሀገር ክህደት ፍጽሞ በሀገር የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመው ተግባርም የቡድኑን አረመኔነት የሚያሳይ ስለመሆኑ አንስተዋል ።
በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ላይ ጥናት የሰሩትና በሚዛን ቲፒ ዩኒቨርሰቲ የህግ መምህርየ አቶ ምንዳ ግርማ በበኩላቸው÷ የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን ያልፈጸመው ኢ ሰብአዊ ድርጊቶች የሉም ሲሉ ገልፀዋል።
በዚህም ሀገሪቱ በአለም ላይ በሰብአዊ መብት አያያዝ ከግርጌ የምትቀመጥ ለዜጎች ድህንነት ስጋት ፈጣሪ አድርጓት አልፏል ብለዋል።
አቶ ምንዳ እንዳሉትም ቡድኑ በፈጸማቸው ኢ- ሰብአዊ ድርጊቶች ሁሉ ተጠያቂ ሊሆን ፤ ዳግም በሀገሪቱ ታሪክ እንዳይደገም ሊታረም ፤ በአለም አቀፍ ወንጀለኝነት ጭምር ሊፈረድ ይገባል ነው ያሉት።
የሰው ልጆች የመኖር መብትን ከመጋፋት ያለፈ ተደጋጋሚ የሀገር ክህደትን የፈጸመው የወንጀለኛ ስብስብን ለፍርድ ለማቅረብ የሚደረገው ጥረትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አንስተዋል ።
በአጠቃላይ በሰብአዊ መብት ላይ የሚሰሩትና የህግ ምሁራኑ እንደሚሉት ህወሓት የጽነፈኛ ቡድን በሀገሪቱ ታሪክ የፈጸማቸው ኢ -ሰብአዊ ተግባራት ሊወገዙ፤ መንግስት ተቋማዊ አሰራሩን በቀጣይ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
በህግ ልእልና የሚያምን ስነ ልቦናን የተላበሰ ፣ትውልድ ማፍራትና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ጥብቅና የሚቆም ዜጋን መፍጠር ላይ ትኩረት እንዲደረግም መክረዋል።
በሀይለየሱስ መኮንን
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.