Fana: At a Speed of Life!

አቶ ልደቱ አያሌው በ30 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተፈቱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ልደቱ አያሌው በ30 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተፈተዋል፡፡
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ወንጀል ችሎት የ30 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ነው ከእስር የተፈቱት።
ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ባሻሻለው ሁለተኛው ክስ ላይ አቶ ልደቱ ያቀረቡትን ዋስትና ጥያቄ ተቀብሏል።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ልደቱ የተሸሻለው ክስ ዋስትና አያስከለክልም ሲል ነው ዋስትናውን የፈቀደላቸው።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.