Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ክህደት እና የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትን በማሳገት  የተጠረጠሩ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሀገር ክህደት እና የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን በማሳገት  የተጠረጠሩ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ከመንግስት እና ህዝብ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል ካደረጉ ፀረ-ሠላም እና ፀረ-ህዝብ የህዋሃት ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ መቀበላቸውን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡

የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው ጥቅምት 24 በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተካሄደውን የእገታ ተግባር እንደመሩና እንዳስተባበሩ በምርመራ የተደረሰባቸው 40 የከዱና በጡረታ የተገለሉ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ አመራሮች ላይ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በዚህም መሰረት ሜጀር ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፣ኮሎኔል በርሄ ወልደ ሚካኤል ገብሩ፣ኮሚሽነር ይህደጎ ስዩም ወልደማርያም ጨምሮ 40 የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።

በመሆኑም መላው የሃገሪቱ ህዝብ በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው ህዋሃት ጥፋት ቡድን አባላት አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በቀጣይም መቐለ ከተማ የገባው የኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን በሚያደርገው አሰሳና ኦፕሬሽን የሚገኙ ውጤቶችን እየተከታተለ በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.