Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ታሪካዊ ቅርሶችን የመጠበቅ እና የህዝብ መዝናኛን የማስፋፋት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታሪካዊ ቅርሶችን የመጠበቅ እና የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች የማስፋፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ።
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እና የከተማው ካቢኔ አባላት የተለያዩ የመዝናኛ ፓርኮችን እና የሼህ ሆጀሌ ቤተመንግሥትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም በከተማዋ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን በመጠበቅ፣ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን በማስፋፋትና ከተማዋን ለመዝናኛነት ምቹ በማድረግ ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ቱሪስቶች ክፍት ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገልጿል።
ጉብኝት ከተካሄደባቸው የመዝናኛ ስፍራዎች መካከል በግንባታ ላይ ያለው ፒኮክ ፓርክ፣ ሆላንድ ፓርክ፣ ህዳሴ ፓርክ እና የሼህ ሆጀሌ ቤተመንግሥት ይገኙበታል።
እነዚህ ታሪካዊ ቅርሶች እና የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች ውስጥ ለማከናወን የታቀዱ የመሠረተ ልማት ግንባታና የእድሳት ስራዎች በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት ገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.