Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የብሉናይል ግዛት በጋራ እንደሚሰሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሱዳን የብሉናይል ግዛት አስተዳደሮች በድንበር አካባቢ ልማትና ሰላም በጋራ ለመስራት በማቀድ የቀጣይ ስድስት ወራት የልማት እና የሠላም ስምምነቶችን ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰንና በሱዳን የብሉናይል ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር አብዱራህማን ኑርአዳኢም ናቸው፡፡
እቅዱ በድንበር አካባቢ ህዝቦችን ተጠቃሚ በማድረግ አንድነታቸውን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ ጸጥታ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ጤና ደግሞ ስምምነቱ ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦች እንደሆኑ የስምምነት ሰነዱ ያስረዳል፡፡
በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተገደበውና በክልሎቹ መካከል የሚገኙ የኩርሙክ፣ ጊዘን፣ አልመሃል እና ባምዛ የጠረፍ ከተሞችን እንቅስቃሴ መልሶ ለማጠናከር እንደሚሰራም ተገልጿል።
በጠረፍ ከተሞቹ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ የነበረውን የግብይት ቀናት ለማሳደግ የክልሎቹ ልኡካን ከሚመለከታው የየአገሮቻቸው ተቋማት ጋር እንደሚነጋሩም ተመልክቷል፡፡
ህገ-ወጥ የደን ጭፍጨፋ፣ ድንበር ዘለል ግብርና፣ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያና የሰዎች እንቅስቃሴ እንዲቆም ክልሎቹ እንደሚሠሩም ተጠቁሟል፡፡
ለሁለት ቀናት በአሶሳ ሲካሔድ ቆይቶ በተጠናቀቀው ስብሰባ ከ50 የሚበልጡ የሁለቱም ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን ልኡካኑ የተፈራረሙት የስምምነት ሰነድም በየአገሮቹ መንግስታት ይሁንታ ሲያገኝ እንደሚተገበር ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.