Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዴንማርክ የልማት ትብብር እና የኖርዲክ ሀገሮች ትብብር ሚኒስትር ፍሌሚንግ ሙለር ሞርትንሰን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከዴንማርክ የልማት ትብብር እና የኖርዲክ ሀገሮች ትብብር ሚኒስትር ፍሌሚንግ ሙለር ሞርትንሰን ጋር የበይነመረብ ውይይት አካሂደዋል።
ሚኒስትሯ ስለተጠናቀቀው የሕግ ማስከበር ሥራ እና በሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ ስላለው ትብብር ገለፃ አድርገዋል፡፡
የሕግ ማስከበር ሥራው ሲቪሎችንና መሠረተ ልማቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ እጅግ በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መከናወኑንም ገልፀዋል።
የልማት ትብብር ሚኒስትሩም በበኩላቸው በሕግ ማስከበር ሂደት ወቅት ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ የተደረገውን ጥረት አድንቀው የዴንማርክ መንግስት የሰብአዊ ፍላጎቶችን ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የወዳጅነት ግንኙነትም የበለጠ እንደሚጠናከር አረጋግጠዋል::
ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የዴንማርክ መንግስት ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን የሰላም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.