Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው -ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአየር ንብረት ላይ ባተኮረው የቪዲዮ ኮንፍረንስ ላይ ተሳትፈዋል።
ዶክተር ዐቢይ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል።
ለጉዳዩ በተሰጠው ትኩረትም በሀገር አቀፍ ጀረጃ የችግኝ ተከላ ስራ መሰራቱን እና ችግኞችን መንከባከቡም መቀጠሉን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነውም ብለዋል።
በዚህም መሠረት እስከ ፈረንጆቹ 2030 ከካርቦን ልቀት ነጻ የሆነ ኢኮኖሚን ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት በአረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከል ወሳኝ ስራ መስራቷን ገልጸዋል።
በ10 አመት የልማት እቅድም አስተማማኝ ኢኮኖሚ ለመገንባት ማቀዷን ነው ያነሱት።
የፓሪስ ስምምነትን በማክበር ሀገራቸው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ የ15 አመት እቅድ መያዟን ተናግረዋል።
በእቅዱ 18 ዘርፎች መለየታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ግብርና፣ የደን ልማት፣ ጤና፣ ትራንስፖርት እና የመሳሰሉት መሆናቸውን አብራርተዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.