Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ኬንያ እና ማላዊ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
ውይይቱ ትናንት ቅዳሜ ህዳር 03 ቀን 2013 ዓ.ም በበይነ መረብ (ቨርቹዋል) ተካሂዷል።
ሀገራችን ከውስጧ በተነሱ ከሃዲዎች ሉዓላዊነታችንን አደጋ ላይ የጣለውን፣ ጭካኔና አሳፋሪ ድርጊት የተፈጸመበትን ሁኔታ ለመለወጥ፣ ህግን ለማስከበር፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ መንግስታችን ያካደሄው ፈጣንና ውጤታማ ተልዕኮ በሕዝባችን ድጋፍና አብሮነት፣ በቁርጠኛው መከላከያ ሠራዊታችን እና ልዩ ልዩ የጸጥታ አካላት አብሮ በመዋደቅ የተገኘው ድል የሁላችንም ድልና ኩራት ነው ብለዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኬንያ እና ማላዊ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዚህ ፈታኝ ጊዜ ላሳዩት ሀገራዊ ስሜት እና ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው መንግስት በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለተሳታፊዎቹ ገልጸውላቸዋል።
በዚህ ኢ-ሰብዓዊና ጭካኔ በተሞላበት ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡም መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንሚሰራም ተናግረዋል።
ክቡር አቶ ደመቀ መንግስት በሚያደገርው ጥረት በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስትና አቋሞች በማስረዳት፣ ለመልሶ ማቋቋሙ እና ዳግም ግንባታው አስተዋጽኦ በማድረግ እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2013 ዓ.ም በጣም ወሳኝ ወቅት መሆኑን በመጥቅስ በኬንያ እና ማላዊ የሚኖሩ ወገኖቻችን የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አገራችን በህወሃት አፍራሽ ሃይል ተገዳ ወደ ህግ ማስከበር መግባቷን ተከትሎ በኬንያ እና ማላዊ የሚኖሩ ወገኖቻችን ላሳዩት የጋለ ብሔራዊ ስሜት እና ላደረጉት ድጋፍ አምስግነዋል።
መንግስት እያካሄደ ያለውን የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ ህገመንግስታዊ ሰርዓቱን የመጠበቅ እና የዜጐችን ደህንነት የማስከበር ዘመቻ እንዲሳካ በኬንያና ማላዊ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች እና ነጋዴዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ጠቅሰው በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው ባላቸው ግንኙነት የህዝብ አምባሳደር ሆነው ስለአገራቸው አቋምና ፍላጐት ዘብ መቆማቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይም ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ፣ የተፈናቀሉትን ለማቋቋም እና የፈረሰውን ለመገንባት መንግስት በሚያደርገው ዳያስፖራው የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ ሚሲዮኑ ሙሉ እምነት እንዳለውም አምባሳደር መለስ ገልጸዋል።
በስነ ሰርዓቱ ላይ የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች የአቋም ያወጡ ሲሆን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ፈጽመዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.