ስፓርት

ዛሬ በተካሄደው ቤት-ኪንግ  የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዳማ ከተማ ጅማ አባጅፋርን ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ አቻ ተለያይተዋል

By Meseret Demissu

December 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ዛሬ በተካሄደው  1ኛ ሳምንት ቤት-ኪንግ  የኢትዮጵያ ፕሪምየር  ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ፣አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር ተጫውተዋል።

በዚህም ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት በተካሄደው  የኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ ጨዋታ 2 ለ 2 አቻ  ወጥተዋል።

9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ አዳማ ከተማ ጅማ አባጅፋርን 4 ለ 1 አሸንፏል።

ሰኞ ረፋድ 4 ሰዓት ላይ ወላይታ ዲቻ ከሀዲያ ሆሳዕና፤ ቀን 9 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ፡፡