Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 441 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ሲያገግሙ 472 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ 1 ሺህ 441 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ሲያገግሙ 472 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 1 ሺህ 441 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 93 ሺህ 890 ደርሷል።

በሌላ በኩል ለ4 ሺህ 799 ሰዎች በተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 472 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 116 ሺህ 769 ደርሷል።

በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 806 መድረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 706 ሺህ 321 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.