ወንጀለኛውን ቡድን ለሕግ የማቅረብ ሥራችን ይቀጥላል -ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከሰዓት በመቐለ ከተማ ተገኝተው ከሀገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች እና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያይተዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው እንደገለጹት የቴሌኮም እና የኤሌክትሪክ ኃይል መሠረታዊ አገልግሎቶች ከጥገና ሥራ በኋላ ተመልሰው እየቀጠሉ ነው።
የመሠረተ ልማት መልሶ ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን፣ ሰብዓዊ እርዳታም እየቀረበ ነው ብለዋል።
ወንጀለኛውን ቡድን ለሕግ የማቅረብ ሥራችን ይቀጥላልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።