Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን በጁንታው ተደብቀው የነበሩ ከ140 በላይ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ፈንጅዎች ተገኙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የጭላ ወረዳ በአንድ አካባቢ ጁንታው ደብቋቸው የነበሩ ከ140 በላይ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ ፈንጅዎችን ጨምሮ በርካታ የከባድ መሳሪያ ተተኳሾች ሰራዊቱ ባደረገው አሰሳ ተገኙ።
በአካባቢው የተሰማራው የ11ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ያሲን ኑርዬ እንደገለፁት፥ ህገወጡ ቡድን ሰራዊቱ አይደርስበትም ብሎ ባሰበው የጭላ ወረዳ ልዩ ስፍራው ሰረፍረፍ በተባለ አካባቢ ስንቅና ትጥቅ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎችን ደብቆ ነበር፡፡
ተሽከርካሪዎቹና ፈንጅዎቹ ሰራዊቱ ባደረገው ህግን የማስሰበር ተግባር መገኘታቸውንም ተናግረዋል።
የ11ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ያረጋል መኮንን በበኩላቸው፥ አካባቢው ከጁንታው አባላት ሙሉ በሙሉ ነፃ በመውጣቱ ህብረተሰቡ ወደቀደመ የተረጋጋ ህይወቱ እየተመለሰ ይገኛል ብለዋል፡፡
በተደረገው አሰሳ ከአምስት በላይ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ተተኳሽ ጥይቶችን የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሶስት መድፍ እና ሮኬቶችን መያዝ ተችሏልም ነው ያሉት፡፡
ይህም የቡድኑን ሌብነት በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።
አሁን ላይም ሰራዊቱ የህብረተሰቡን ሰላም ከማስጠበቅ አንፃር በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በፋሲካው ታደሰ
ተጨማሪ መረጃ ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.