Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ እስካሁን ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ እስካሁን ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል ገለጸ፡፡

በአፍሪካ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እስካሁን ከ55 ሺህ 900 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ማዕከሉ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በአህጉሪቱ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን 361 ሺህ በላይ መሆኑም ነው የገለጸው፡፡

በአንጻሩ ከ2 ሚሊየን 4 ሺህ 900 በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውም ተነግሯል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ፣ ሞሮኮ እና ግብጽ ደግሞ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት መካከል በቀዳሚነት ተጠቅሰዋል፡፡

ደቡባዊ እና ሰሜናዊ የአፍሪካ ክልሎች ከአህጉሪቱ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ከጸናባቸው ሃገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.