Fana: At a Speed of Life!

የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አምብሮሲ ድላሚኒ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአራት ሳምንታት በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ገልጸው በመልካም ጤንነት ላይ ይገኙ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ሆኖም የ52 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በደቡብ አፍሪካ ሆስፒታል ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ትናንት ከሰዓት ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን የመጡት በፈረንጆቹ 2018 ጥቅምት ወር ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የአሁኗ ኢስዋቲኒ የቀድሞዋ ስዋዚላንድ ንጉስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

 

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.