Fana: At a Speed of Life!

ህግን ያላከበሩ 812 የንግድ ተቋማት የንግድ ፈቃዳቸው ሲሰረዝ 40 ሺህ 823 ተቋማት ታሽገዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመላ ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራቶች ህግን ባላከበሩ የንግድ ተቋማት እርምጃ መወሰዱን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል አስታወቁ።

በዚህም በአምስት ወራቱ ህግን ያላከበሩ 812 የንግድ ተቋማት የንግድ ፈቃዳቸው እንደተሰረዘ ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ህግን ባላከበሩ 58 ሺህ 423 የንግድ ድርጅቶች ላይም ማስጠንቀቂያ መፃፉን አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም 40 ሺህ 823 የንግድ ተቋማት የታሸጉ ሲሆን በ324 ተቋማት ላይ ክስ ሲከፈት በ90 ተቋማት ላይ ደግሞ የእገዳ እርምጃ ተወስዷል ነው ያሉት::

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.