Fana: At a Speed of Life!

በቤልጂየም እና በሉክዘምበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህግ በማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤልጂየም እና በሉክዘምበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህግ በማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከ799 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

በትናንትናው ዕለት በቤልጂየም እና በሉክዘምበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በትግራይ ክልል ህግ በማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ለድጋፍ ማሰባሰቢያ ተብለው በተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች ከ799 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማድረጋቸው እና ቃል መግባታቸው ተጠቁሟል።

ከዚህ ውስጥ 229 ሺህ 617 ብር ውይይቱ ከመካሄዱ በፊት ድጋፍ የተደረገ እና ቃል መገባቱን በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በበይነ መረብ አማካኝነት በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለታደሙት ተሳታፊዋች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ አማካኝነት ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ እንደተናገሩት “በተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉትንና ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም በመንግስት እየተደረገ ያለው ጥረት እንዳለ ሆኖ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የበኩላቸውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ለወገን ደራሽ ወገን ነው ያሉት አምባሳደሯ በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍን ይሻሉ ብለዋል፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በሙሉ ልብ እንደሚደግፉ ጠቅሰው በሂደቱም በከፍተኛ መነሳሳት ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን ለማሳየት ለዚሁ ዓላማ በተከፈቱት የሂሳብ ቁጥሮች አማካኝነት በቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.