የሀገር ውስጥ ዜና

የሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ እንደ ሀገር ዝቅተኛ መሆኑ ተገለፀ

By Feven Bishaw

December 14, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ እንደ ሀገር ዝቅተኛ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ነቢል መህዲ በአሁኑ ጊዜ የሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ እንደ ሀገር ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሴት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ከማምጣት ባሻገር በትምህርት ገበታቸው እንዲቆዩና ለውጤት እንዲበቁ አሁንም ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን እና የትምህርት ተቋማት ለሴት ተማሪዎች ምቹና ከትንኮሳ የፀዱ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ወሲባዊ፣ አካላዊና ስነ ልቦናዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶችን ለመቅረፍ ሁሉም ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይገባዋል መባሉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡