Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5፤ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

ውይይቱ በኢሊሊ ሆቴል ባለሃብቶች በክልል መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ነው የተካሄደው፡፡

በመድረኩ በክልሉ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታ መኖሩ ተነስቷል፡፡

የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መንግስት ለባለሃብቱ አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመኑን ገልጿል፡፡

በዚህም ባለሃብቱ ብድር እንዲመቻችለትና ማሽኖችን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገባ እንዲሁም ማነቆ የነበሩ ህጎችን ማሻሻሉን የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮርፖሬሽን ዋና ሃላፊ ሲሳይ ገመቹ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የገዳ ልዩ ዞን ኢንዱስትሪ ፓርክ ተዋውቋል፡፡

ከተቋቋመ አራት አመት የሆነው የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን በክልሉ ቡልቡላ ኢንዱስትሪ ፓርክ ላይ 280 ሄክታር እያለማ ይገኛል፡፡

ፓርኩ 10 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን፤ ከ70 ሺህ እስከ 100 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ተብሏል፡፡

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.