Fana: At a Speed of Life!

የኦነግ ሸኔ ፀረ ሰላም ሀይል እየተዳከመ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦነግ ሸኔ ፀረ ሰላም ሀይል እየተዳከመ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ከፋና ብድሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ በዋናነት ለኦነግ ሸኔ የሎጅስቲክስ ድጋፍ ሲያደርግ የነበረው የጁንታው ሀይል በመደምሰሱ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ላይ አባ ቶርቤ በሚል ስያሜ ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ የነበረውም ሆነ በጫካ ውስጥ የመሸገው ኦነግ ሸኔ እየተዳከመ መሆኑን ገልፀዋል።

የኦነግ ሸኔንም ሆነ አባ ቶርቤን ከፌደራል የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

አሁን ላይ በአባ ቶርቤ ስም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በመንቀሳቀስ የሰው ህይወት እንዲጠፋና እና መሰል ጥቃቶች እንዲፈፀሙ በማደራጀት እና ወንጀሉን በመምራት ሲሰሩ የነበሩ ዘጠኝ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

በተመሳሳይ በጫካ ውስጥ ያለውን የኦነግ ሸኔ ፀረ ሰላም ሀይል ሲመሩ የነበሩ እና ለፀረ ሰላም ሀይሉ የተለያዩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ 116 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች በአባ ቶርቤ ስም ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩም ሆነ በጫካ ውስጥ መሽጎ እየተንቀሳቀሰ ያለው ፀረ ሰላም ሀይሉ ኦነግ ሸኔ አሁን ላይ ከጁንታው ይቀርብላቸው የነበረው የቀለብ፣ የሰው ሀይል፣ የስልጠና ፣ የትጥቅ እና መሰል ሎጅስቲክስ በመቅረቱ የመጨረሻ አቅማቸውን እየተጠቀሙ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

ይህ ሀይል ህዝብ ውስጥ መሽጎ የሚንቀሳቀስ በመሆኑም ሙሉ በመሉ ከህዝቡ ተነጥሎ እንዲወገድ እና የክልሉ ሰላም እንዲረጋገጥ ህዝቡ ወንጀለኞችን አሳልፎ እንዲሰጥ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ጥሪ አቅርበዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.