Fana: At a Speed of Life!

ለአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ዋና መስሪያ ቤት የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ለአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል /ሲዲሲ/ ዋና መስሪያ ቤት የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገነባው የማዕከሉ ህንጻ ወጪው በቻይና መንግስት የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ በአፍሪካ ህብረት የማህበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽን ኮሚሽነር አሚራ ኢልፋዲል ሞሃመድ፣ በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደር ሊኡ ዩጂ፣ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የሲዲሲ አፍሪካ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ መገንባት አፍሪካውያን የኮቪድ -19፣ የኢቦላ እና ሌሎች ወረርሽኞችን አስቀድሞ ለመከላከል እና የምርምር ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል በአፍሪካ ህብረት የማህበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽን ኮሚሽነር አሚራ ኢልፋዲል ሞሃመድ ገልጸዋል።
ማዕከሉ 90 ሺህ ስኩዌር ሜትር በሆነ ቦታ ላይ እንደሚያርፍም ተገልጿል፡፡
ማዕከሉ በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.