Fana: At a Speed of Life!

በኢንስቲቲዩቱ የሚገኘው አላስፈላጊ የኬሚካል ክምችት መወገድ እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት የሚገኘው አላስፈላጊ የኬሚካል ክምችት መወገድ እንዳበት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ይህንን ያሳሰበው በምርምር ኢንስቲቲዩቱ የመስክ ምልከታ ማካሄዱን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በምልከታውም ኢንስቲቲዩቱ ለምርምር ስራ የላቦራቶሪ ኬሚካሎችን የሚጠቀም መሆኑንና ነገር ግን መወገድ ሲገባው ያልተወገደ የኬሚካል ክምችት መኖሩን አረጋግጧል፡፡

በኬሚካል ክምችት ምክንያት በሌሎች ሃገራት የተከሰተው አደጋ በኢትዮጵያ ከመከሰቱ በፊት ኢንስቲቲዩቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በአስቸኳይ ማስወገድ እንዳለበት የቡድኑ አስተባባሪ ወይዘሮ ባንቹ ሙሉጌታ አሳስበዋል፡፡

የኢንስቲቲዩቱ የምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ድሪባ ገለቲ በበኩላቸው የኬሚካል ክምችቱን ለማስወገድ አንድ ጠንካራ ሃገራዊ ተቋም እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.