Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል- ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደትን ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው የአየር ክልል ከዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የዓለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ነው ባለስልጣኑ የገለፀው።

አገልግሎት መሥጠት የሚችሉ አውሮፕላን ማረፊያዎች በረራ ማስተናገድ የሚችሉ መሆኑም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.