Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 473 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 335 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 778 የላብራቶሪ ምርመራ 473 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው እንደገለጹት 1 ሺህ 335 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 3 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 95 ሺህ 225 ሲደርሱ 1 ሺህ 809 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 20 ሺህ 206 ሲሆኑ 297 ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 711 ሺህ 99 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡

ከነዚህ መካከልም 117 ሺህ 242 በወረርሽኙ የተያዙ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 20 ሺህ 206 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.